Download
Download is available until [expire_date]
  • Version
  • Download 300
  • File Size 36.00 KB
  • File Count 1
  • Create Date October 19, 2023
  • Last Updated October 20, 2023

የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሁለተኛውን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ባለ 60 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ሁለተኛው የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት ኮሚሽኑ የተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ ሁኔታዎችንና ምክረ ሐሳቦችን አካቷል።

ኢሰመኮ በአፋር፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሶማሊ ክልሎች በግጭት እና ሌሎች ሰው ሠራሽ መንሥዔዎች የተፈናቀሉ ከ363 ሺ በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን፣ ተመላሾችን እና ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ የተደረጉ ተፈናቃዮችን የሚያስጠልሉ 62 መጠለያዎችን፣ ጣቢያዎችን እና ተቀባይ ማኅበረሰቦችን በመድረስ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አያያዝ ላይ ክትትሎች እና ምርመራዎችን በማካሄድ ሪፖርቱን አጠናቅሯል። ሪፖርቱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ምዝገባ እና ሰነድ የማግኘት መብት፣ የጸጥታና ደኅንነት፣ የመንቀሳቀስ መብት፣ የሰብአዊ ድጋፍ የማግኘት መብት እንዲሁም ለሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኛ ተፈናቃዮች የሚደረግ ልዩ ድጋፍ እና በአጠቃላይ የዘላቂ መፍትሔዎች አተገባበር ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ ስምምነትን (የካምፓላ ስምምነት) ካጸደቁ 33 የአፍሪካ ሀገራት አንዷ ስትሆን፣ ስምምነቱ ብሔራዊ ሕግ እና ተቋማዊ መዋቅር እንዲኖር ማስቻልን ዋነኛ የመንግሥት ኃላፊነት በማድረግ በደነገገው መሠረት ስምምነቱን ማስፈጸሚያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች የተደረጉ መሆኑን በሪፖርቱ እንደ አንድ ቁልፍ እመርታ ተካቷል።

የሪፖርቱ አንኳር ጉዳዮች