Download
Download is available until [expire_date]
  • Version
  • Download 28
  • File Size 44.00 KB
  • File Count 1
  • Create Date March 5, 2024
  • Last Updated April 9, 2024

በጋምቤላ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ወቅቶች በተከሰቱ ግጭቶች እና የጸጥታ መደፍረስ ሁኔታዎች ሳቢያ የደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የተደረገ የምርመራ ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ ጎግ ወረዳ እና ጋምቤላ ከተማ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. አንስቶ በተከሰቱ ግጭቶች እና የጸጥታ መደፍረስ የተነሳ በደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ላይ ከመስከረም 20 እስከ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ያከናወነውን ምርመራ እንዲሁም ከመስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በኋላ በደረሱ ጥቃቶች ዙሪያ እና በመንግሥት የተወሰዱ እርምጃዎችን አስመልክቶ ተጨማሪ ክትትል በማድረግ ያሰባሰባቸውን መረጃዎች እና ማስረጃዎች የሚያካትት ባለ 15 ገጽ የምርመራ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ኢሰመኮ ግጭት ወደተከተሰባቸው ቦታዎች በአካል በመሄድ ከተጎጂዎች፣ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከዐይን ምስክሮች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ቃለ መጠይቆች እና የቡድን ውይይቶች አድርጓል፡፡ በተጨማሪም በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ መንግሥት የጸጥታና አስተዳደር አካላትን እንዲሁም የፌዴራል ተቋማትን በማነጋገር መረጃዎችንና ማስረጃዎችን አሰባስቧል።