- Version
- Download 227
- File Size 36.00 KB
- File Count 1
- Create Date July 12, 2023
- Last Updated November 7, 2023
አንኳር ጉዳዮች:- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት (ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም.)
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው ይህ ሪፖርት ኮሚሽኑ ባደራጃቸው ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች እና የከተማ ጽሕፈት ቤቶች አማካኝነት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በጥቅሉ የሚዳስስ ነው፡፡ ሪፖርቱ ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በለያቸውና በሚሠራባቸው የትኩረት ዘርፎች (Thematic Areas) ላይ መሠረት ያደረገ ሲሆን በሪፖርቱ ውስጥ በዝርዝር ከተተነተኑት አንኳር ጉዳዮች መካከል የተወሰኑት እንደሚከተለው ቀርበዋል።
በሪፖርት ዘመኑ ከተመዘገቡ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ማሻሻል የሚያስችሉ ቁልፍ ክስተቶች እና እመርታዎች መካከል በዋናነት በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው ጦርነት በደቡብ አፍሪካ በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕዋሓት) መካከል የዘላቂ ተኩስ ማቆም እና ሰላም ስምምነት መፈረሙ፤ ይህንንም ተከትሎ የፌዴራል መንግሥት በፍትሕ ሚኒስቴር ሥር ባደራጀው የባለሙያዎች ቡድን ረቂቅ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጮች (Green Paper) ማዘጋጀቱ እና ማኅበረሰብ አቀፍ ውይይቶች መካሄድ መጀመራቸው፤ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልል አብዛኛው አካባቢዎች ሰላም የሰፈነ መሆኑ እና በተወሰነም ደረጃ የሚታዩ የመልሶ ግንባታ፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መሻሻል፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ጥረቶች መጀመራቸው ይጠቀሳል፡፡
በተጨማሪም በኮሚሽኑ ክትትል እና ምክረ ሐሳብ መሠረት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በፈጸሙ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ሕጋዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ረገድ በሁሉም ክልሎች የሚታዩ ጅማሮዎች መኖራቸው አበረታች ነው፡፡ ኮሚሽኑ በሚሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች መሠረት ለእስር ወይም ለአስገድዶ መሰወር የተዳረጉ ሰዎች ሲፈቱ፣ አቤቱታ ያቀረቡ ሰዎች እልባት ሲያገኙ እንዲሁም አሠራሮች ሲዘረጉ እና የፖሊሲ እና የሕግ ማሻሻያ ሥራዎች ሲጀመሩ ታይተዋል።
- ሙሉ ሪፖርቱ እዚህ ተያይዟል
- Executive Summary: Ethiopia Annual Human Rights Situation Report (June 2022 – June 2023)