- Version
- Download 27
- File Size 309.29 KB
- File Count 1
- Create Date June 6, 2023
- Last Updated August 22, 2023
አንኳር ጉዳዮች:- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የተደራሽነት ሁኔታ ክትትል ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማድረግ አንዱ በመሆኑ፤ በተለይ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ የክትትል ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ በዚህም መሠረት ኮሚሽኑ የአካል ጉዳተኞች የከፍተኛ ትምህርት ተካታችነትን ሁኔታ ለመፈተሽ ያስችለው ዘንድ የኢትዮጵያ የሕግ እና የፖሊሲ ማዕቀፎች እንዲሁም አጠቃላይ ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣ የመረጃ እና የአመለካከት ተደራሽነትን ለመገምገም የሚረዳ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ከነሐሴ 10 እስከ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ ሐረማያ፣ ሀዋሳ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከነሐሴ 17 እስከ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ዳግም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አከናውኗል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ክትትሉ በተደረገበት ወቅት የተፈለገውን ያህል መረጃ ባለመገኘቱ እንዲሁም መካተት የነበረባቸው ነገር ግን ከጊዜ አንፃር ያልተዳሰሱ ቦታዎችን እንዲሁም ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት ተከታታይ ክትትል በተለያዩ ጊዜያት ተካሂዷል፡፡