- Version
- Download 47
- File Size 611.14 KB
- File Count 1
- Create Date August 26, 2023
- Last Updated September 14, 2023
አንኳር ጉዳዮች:- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝበ ውሳኔ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን እና ኃላፊነቶች መካከል አንዱ በምርጫ ወቅት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ማድረግ በመሆኑ በቀድሞው ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት (የቀድሞው ደቡብ ክልል) ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የተደረገ ሕዝበ ውሳኔ እንዲሁም በወላይታ ዞን ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የተደረገ ድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ ሂደትን የሰብአዊ መብቶች ክትትል አድርጓል። ሕዝበ ውሳኔው የተደረገው በቀድሞው ደቡብ ክልል ስድስት ዞኖች (ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ወላይታ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (አሌ፣ አማሮ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ እና ዲራሼ) የሚገኙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች አዲሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለመመሥረት ባቀረቡት ጥያቄና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዴ.ሪ) ፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት ነበር፡፡
የኮሚሽኑ ክትትል በሕዝበ ውሳኔ ወቅት ለሚከሰቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የውትወታ ሥራዎችን መሥራት፤ ሕዝበ ውሳኔው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ እና የድምፅ መስጠት ሂደቱ ለሰብአዊ መብቶች መስፈርቶች የነበረውን ተገዢነት የመገምገም፤ በሕዝበ ውሳኔ ጊዜ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች እና ተግዳሮቶችን በመሰነድ ወደፊት የሚደረጉ ሕዝበ ውሳኔዎች ወቅት የተሻለ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ባህል እንዲጎለብት አስተዋጽዖ ማድረግ ዓላማን የያዘ ነው።