Download
Download is available until [expire_date]
  • Version
  • Download 21
  • File Size 365.18 KB
  • File Count 1
  • Create Date July 7, 2023
  • Last Updated August 18, 2023

አንኳር ጉዳዮች:- ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት፡ የግንባታ ዘርፍ ክትትል ሪፖርት

“የሙያ ደኅንነት እና ጤንነት ወጪዎች እንደ ኪሳራ ወጪዎቹን መቀነስ ደግሞ እንደ ትርፍ ይቆጠራል”

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብትን በተመለከተ የግንባታ ሥራ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ባለ 36 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት ያለምንም መድልዎ በማንኛውም የሥራ ዘርፍ እና የቅጥር ዓይነት ለሚሠሩ ሠራተኞች የተሰጠ መብት ሲሆን፣ ከፍትሐዊ እና ምቹ የሥራ ሁኔታዎች መብት መሠረታዊ ክፍሎች መካከል አንዱ እና ከሌሎች መብቶች በተለይም ከአካላዊ እና አእምሯዊ ጤና መብት ጋር የተቆራኘ ነው። የግንባታ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ የሥራ ላይ አደጋዎች የሚከሰቱበት እና ለደኅንነት እና ለጤንነት አስጊ ከሆኑ ዘርፎች መካከል በመሆኑ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት ላይ ሀገር አቀፍ የሕግና ፖሊሲ ማዕቀፎችን እና አተገባበራቸውን ለመፈተሽ ጥሩ ማሳያ ነው።

ሪፖርቱን ለማዘጋጀት በአጠቃላይ ከ182 ሰዎች መረጃ፣ ሰነዶች እና ማስረጃዎች የተሰበሰቡ ሲሆን፣ 44 ከሚመለከታቸው የመንግሥት ቢሮዎች፣ 33 ከሕንጻ ተቋራጮች፣ 72 የግንባታ ሠራተኞች እና 10 ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተሳተፈዋል። በተጨማሪም በጉዳዩ ላይ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ የተለያዩ ተቋማትን እና ባለድርሻዎችን የወከሉ 23 ተሳታፊዎች ተካተዋል፡፡ ክትትሉ በአዳማ፣ በአዲስ አበባ፣ በባሕር ዳር፣ በሃዋሳ እና በጅግጅጋ ከተሞች የተደረገ ነው።

⬇️ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት፡ የግንባታ ዘርፍ ክትትል ሪፖርት