Download
Download is available until [expire_date]
  • Version
  • Download 114
  • File Size 2.65 MB
  • File Count 1
  • Create Date October 25, 2024
  • Last Updated October 28, 2024

የሴቶች እና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት (ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም.)

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሦስተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የሴቶች እና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። ይህ የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በተጨማሪነት የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ በዝርዝር በማተኮር በበጀት ዓመቱ የለያቸውን አበረታች እመርታዎች፣ አሳሳቢ ጉዳዮች እና ምክረ ሐሳቦችን አካቷል፡፡

ሪፖርቱ የተዘጋጀው ኢሰመኮ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ክትትሎችና ምርመራዎች፣ የአካል ምልከታዎች፣ የቀረቡ አቤቱታዎች፣ የሕግና የፖሊሲ ግምገማዎች፣ ምክክሮች እንዲሁም የውትወታ ሥራዎችን መሠረት በማድረግ ነው።

በግጭት እና ድኀረ ግጭት ወቅት የሴቶች እና የሕፃናት የጤና መብቶች፣ በግጭት ዐውድ ውስጥ ከጾታዊ እና ወሲባዊ ጥቃቶች የመጠበቅ መብት፣ በድኀረ ግጭት ወቅት የአካል ጉዳተኛ ሴቶች እና ሕፃናት መብቶች፣ የተፈናቃይ ሴቶች እና ሕፃናት መብቶች፣ የትምህርት መብት፣ ሕፃናትና ታዳጊዎች ከጥቃት እና ከጉልበት ብዝበዛ የመጠበቅ መብቶች፣ በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝ፣ ከእናቶቻቸው ጋር በማቆያ/በማረሚያ ቤት የሚገኙ ሕፃናትን ጨምሮ የሴት ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች አያያዝ፣ የወላጆቻቸውን እንክብካቤ ማግኘት ያልቻሉ ሕፃናት እንዲሁም በሰፋፊ የእርሻ ልማቶች ውስጥ የሚሠሩ የሴቶች እና የታዳጊዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርቱ በዋናነት ትኩረት ያደረገባቸው ጉዳዮች ናቸው።

የሪፖርቱ አንኳር ጉዳዮች እዚህ ተያይዟል