- Version
- Download 42
- File Size 1.18 MB
- File Count 1
- Create Date May 13, 2024
- Last Updated May 13, 2024
የተባበሩት መንግሥታት የንግድ እና ሰብአዊ መብቶች መመሪያ መርሖች
አጠቃላይ መርሖች
እነዚህ የመመሪያ መርሖች፡-
(ሀ) ሰብአዊ መብቶችን እና መሠረታዊ ነጻነቶችን የማክበር፣ የመጠበቅና የማሟላት ነባር የመንግሥት ግዴታዎችን፤
(ለ) የንግድ ድርጅቶች እንደ ልዩ የኅብረተሰብ አካል ልዩ ተግባራትን የማከናወን ሚና ሲወጡ ሁሉንም የሚመለከታቸው ሕጎችን እና ሰብአዊ መብቶችን በማክበር እንዲሆን ተጠባቂነትን፤
(ሐ) መብቶች እና ግዴታዎች በሚጣሱበት ጊዜ ተገቢና ውጤታማ ከሆኑ መፍትሔዎች ጋር እንዲጣጣሙ የማድረግ አስፈላጊነትን ዕውቅና በመስጠት የተመሠረቱ ናቸው።
እነዚህ የመመሪያ መርሖች ለሁሉም ሀገራት እና መጠናቸው፣ የተሰማሩበት ዘርፍ፣ ቦታቸው፣ ባለቤትነታቸው እና መዋቅራቸው ምንም ይሁን ምን ለሁሉም ድንበር ተሻጋሪ እና ሌሎች የንግድ ድርጅቶች ተፈጻሚ ይሆናሉ።
እነዚህን የመመሪያ መርሖች አንድ ወጥነት ባለው መልኩ መረዳት እና በተናጠልም ሆነ በጋራ ሲነበቡ ከንግድ እና ሰብአዊ መብቶች ጋር በተያያዘ ደረጃዎችን እና አሠራሮችን በማጎልበት ለተጎዱ ግለሰቦች እና ማኅበረሰቦች ተጨባጭ ውጤቶችን ለማምጣት እና በዚህም ማኅበራዊ ዘላቂነት ላለው ግሎባላይዜሽን አስተዋጽዖ በሚያደርግ መልኩ መሆን አለበት።
እነዚህ የመመሪያ መርሖች አዲስ የዓለም አቀፍ ሕግ ግዴታዎችን እንደሚፈጥሩ፣ ወይም አንድ ሀገር ሰብአዊ መብቶችን በሚመለከት በዓለም አቀፍ ሕግ የገባውን ወይም የተጣለበትን ማንኛውንም ሕጋዊ ግዴታን የሚገድብ ወይም የሚያዳክም ተደርጎ መነበብ የለበትም።
እነዚህ መመሪያ መርሖች ከፍተኛ የተጋላጭነት ወይም የመገለል ሥጋት ሊደርስባቸው የሚችሉ ቡድኖች ወይም ሕዝቦች አባል የሆኑ ግለሰቦችን መብቶች እና ፍላጎቶች፣ እንዲሁም የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን የተለየ ትኩረት በሰጠ፣ እና በሴቶች እና በወንዶች ላይ ሊደርሱ ስለሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ያለአድልዎ መተግበር አለባቸው።