- Version
- Download 58
- File Size 1.23 MB
- File Count 1
- Create Date December 19, 2024
- Last Updated December 19, 2024
የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ለአካል ጉዳተኞች ያለው የተደራሽነት ሁኔታ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ለአካል ጉዳተኞች ያለው ተደራሽነት ላይ ያተኮረ ባለ 30 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል። በሪፖርቱ የተስተዋሉ መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ ጉዳዮች፣ የአካል ጉዳተኛ መንገደኞች ተሞክሮ፣ ዝርዝር ምክረ ሐሳቦች እና ክትትሉ ከተከናወነ በኋላ የተስተዋሉ ለውጦች እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠውን ምክረ ሐሳብ ለመተግበር የሰጠው የጽሑፍ ምላሽ ተካተዋል።