- Version
- Download 75
- File Size 1.11 MB
- File Count 1
- Create Date August 26, 2023
- Last Updated September 14, 2023
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝበ ውሳኔ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቀድሞው ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የሚገኙ 6 ዞኖች (ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ወላይታ) እና 5 ልዩ ወረዳዎች (አሌ፣ አማሮ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ እና ዲራሼ) የተደረገ ሕዝበ ውሳኔ እንዲሁም በወላይታ ዞን የተደረገ ድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ ላይ ያከናወነውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ባለ 50 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።
ክትትሉ ከታኅሣሥ 26 እስከ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅድመ ሕዝበ ውሳኔ፤ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሕዝበ ውሳኔ ዕለት እንዲሁም ከጥር 30 እስከ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. የተካሄደውን የድኅረ-ሕዝበ ውሳኔ በተመረጡ አካባቢዎች በአካል በመገኘት የተከናወነ ነው። በተጨማሪም በወላይታ ዞን የተደረገው የድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ ሂደት ላይ ከግንቦት 30 እስከ ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅድመ ሕዝበ ውሳኔ ክትትል፣ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የሕዝበ ውሳኔ ዕለት ክትትል እንዲሁም ሰኔ 13 እና 14 የድኅረ ሕዝበ ውሳኔ ክትትል አከናውኗል።