- Version
- Download 60
- File Size 851.91 KB
- File Count 1
- Create Date May 29, 2024
- Last Updated May 29, 2024
የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች አተገባበር ላይ የተሰጡ ምክረ ሐሳቦችን በተመለከተ የተከናወነ የትግበራ ክትትል ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኅዳር ወር 2015 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች አተገባበር የክትትል ሪፖርት ላይ ያቀረባቸውን ምክረ ሐሳቦች ተፈጻሚነት አስመልክቶ ከመስከረም 6 እስከ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. የትግበራ ክትትል በማከናወን ያዘጋጀውን ባለ 12 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
ኢሰመኮ በዚህ የትግበራ ክትትል በዋናው የክትትል ሪፖርት የተጠቆሙ ምክረ ሐሳቦች ያሉበትን የአተገባበር ሁኔታ ለመገምገም እንዲሁም ከክትትሉ በኋላ የተፈጠሩ ክፍተቶች ካሉ ለመለየት አልሞ የተነሳ ሲሆን፣ ይህንኑ ከግብ ለማድረስ ገላጭ የክትትል ዘዴን (qualitative follow-up methodology) ተጠቅሟል። በአዲስ አበባ፣ በሃዋሳ እና ጅማ ከተሞች ከሚገኙ የኤጀንሲ ሠራተኞች፣ የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች፣ ተጠቃሚ ድርጅቶች፣ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት እና ሌሎች ባላድርሻ አካላት በአጠቃላይ ከ57 ተሳታፊዎች ጋር በተደረጉ ቃለ መጠይቆች፣ በአካል ምልከታ እና በሰነዶች ትንተና መረጃዎች እና ማስረጃዎችን አሰባስቧል።