Download
Download is available until [expire_date]
  • Version
  • Download 6
  • File Size 603.77 KB
  • File Count 1
  • Create Date May 4, 2025
  • Last Updated May 4, 2025

ማብራሪያ:- የፕሬስ ነጻነት

የተ.መ.ድ. ጠቅላላ ጉባኤ እ.ኤ.አ. 1993 የፕሬስ ነጻነት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በየዓመቱ እ.ኤ.አ. ግንቦት 3 ቀን ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት ቀን ይከበራል።

በዚህ ዓመት ትኩረቱን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial intelligence) በፕሬስ ነጻነት እና በመገናኛ ብዙኃን ላይ እያሳደረ ያለው ተጽዕኖ ላይ በማድረግ ፖሊሲ አውጪዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በጎ ካልሆኑ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ተጽዕኖዎች ይልቅ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ለፕሬስ ነጻነት እና ለዴሞክራሲ እድገት የሚያበረክተውን በጎ አስተዋፆ ማረጋገጥ ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን ሚያዝያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ግንቦት 3 ቀን 2025) በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ32ተኛ ጊዜ በብራስልስ ከተማ ተከብሯል። ይህ ማብራሪያ ይህንኑ ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን የፕሬስ ነጻነትን በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር ይረዳል።