- Version
- Download 6
- File Size 770.11 KB
- File Count 1
- Create Date October 9, 2024
- Last Updated October 9, 2024
የፖሊሲ መግለጫ:- በኢትዮጵያ የአረጋውያንን ሰብአዊ መብቶች ለማሳደግ የማኅበራዊ ጥበቃ ሥርዓት ማጠናከሪያ ስትራቴጂ
አጭር የፖሊሲ መግለጫ:- በኢትዮጵያ የአረጋውያንን ሰብአዊ መብቶች ለማሳደግ የማኅበራዊ ጥበቃ ሥርዓት ማጠናከሪያ ስትራቴጂ
እ.ኤ.አ. በ2023 የወጣው የዓለም ማኅበራዊ ሪፖርት የዓለማችን ሕዝብ ዕድሜ መግፋት ሁኔታ/አዝማሚያ የማይቀለበስ መሆኑን እና ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በሚቀጥሉት ሦስት አስርት ዓመታት ውስጥ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ቁጥር ፈጣን እድገት የሚመዘገብበት መሆኑ እንደሚጠበቅ ይገልጻል (የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት)። በዚህ ሪፖርት መሠረት “የጤና እንክብካቤ፣ የረጅም ጊዜ እንክብካቤ፣ የጡረታ እና የሌሎች ከዕድሜ መግፋት ጋር የተያያዙ የድጋፍ ወጪዎች መጨመር፤ መንግሥት የሚሰበስበው ገቢ በሥራ ዕድሜ ላይ ያሉ ግብር ከፋዮች ጥቂት በመሆናቸው ምክንያት በየጊዜው እየቀነሰ መሄዱ ተደምሮ ዕድሜው የገፋው የማኅበረሰብ ክፍል የበጀት ተግዳሮቶች ሊያጋጥመው ይችላል (ዝኒ ከማሁ)። ይህ አጭር የፖሊሲ መግለጫ በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ የማኅበራዊ ጥበቃ ሁኔታ በመዳሰስ እና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመለየት ለአረጋውያን አካታች እና ጠንካራ የሆነ ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችሉና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ምክረ ሐሳቦችን ይሰጣል።
Policy Brief: Strategies to Strengthen the Social Protection System to Enhance the Human Rights of Older Persons in Ethiopia