. . . ሀገራችን በምትገኝበት ፈታኝ ጊዜ ውስጥም ጭምር እና በሥራ ላይ ባሉ የትምህርት ተቋማት ውስጥ፣ ትምህርት ቤቶች ልጆቻችን መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች መርሆችን፣ አብሮ መኖርን እና መዋደድን የሚያዩበትና የሚኖሩበት እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል። ይህ እንዲሆን የትምህርት ተቋማቶች ከአነሳሽ፣ ግጭት ጠንሳሽ ንግግሮች የጸዱ እንዲሆኑ ማድረግ፣ ይልቁንም ተቋማቱ ልጆቻችን ሊሄዱ የሚጓጉበት እና የተሳትፎ፣ የፈጠራና የመዝናኛ ጊዜ የሚያገኙበት፣ እንዲሁም በሥነ ምግባራቸውና በአሠራራቸው ምሳሌ የሚሆኗቸውን ሰዎች የሚያዩበት ቦታ እንዲሆኑ ማድረግ ተጨማሪ ሃብትም ሆነ የተራዘመ ዕቅድ አይጠይቅም። ስለሆነም፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባልደረቦቼ ስም በተቋማችን ላይ የተጣለውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የአቅማችንን ሁሉ እንደምናደርግ ስገልጽ ለሁሉም ወገኖች ይህንን የሰላም ጥሪ እና መልካም ምኞት በማስተላለፍ ነው።
This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.