በዚህ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሲቪልና የፖለቲካ እንዲሁም የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጅብሪል ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት፥ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዉን ተከትሎ ለግል ድርጅት ተቀጣሪ ሰራተኞችም የደሞዝ ማሻሻያ መደረጉ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል
የታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች በተሟላ ሁኔታ እንዲከበሩ ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በተጨማሪ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ አስተዋጽዖ ሊያደርጉ ይገባል
መንግሥት የሠራተኛውን ሕዝብ ጤንነት፣ ደኅንነትና የኑሮ ደረጃ ለመጠበቅ መጣር አለበት
Government shall endeavour to protect and promote the health, welfare and living standards of the working population of the country
በተለይም ሴት ሕፃናት የመማር መብታቸውን ከማጣታቸው አልፎ ለ ያለ ዕድሜ ጋብቻ እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲሁም ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸው፣ ወደ ከተማ እየፈለሱና ለጉልበት ብዝበዛ እየተዳረጉ መሆኑን ኮሚሽኑ አመልክቷል
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ባሉ ግጭቶች እና በሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ ከ5500 በላይ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራቸውን ከማከናወን ውጪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ
ኢሰመኮ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች መካከል በፖሊስ ጣቢያዎች እና በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎችን የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን በተመለከተ የመከታተልና ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ ከተቋሙ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል
የታራሚዎችንና የተጠርጣሪዎችን ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ለማሻሻል ምክረ ሐሳቦችንና የተደረሱ ስምምነቶችን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መተግበር ያስፈልጋል
የ2017 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን መቃረብን ከግንዛቤ ያስገባ ፈጣን እና የተቀናጀ የመፍትሔ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው
በተለይም ግጭት ባለባቸው በኦሮሚያ፣ አማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በታጣቂዎች በሚፈጸም ጥቃት እና መንግሥት ያንን ለመከላከል አልያም ለፍትሕ ለማቅረብ በሚደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ንፁሐን እየሞቱ እና እየተጎዱ መሆኑን መንግሥታዊው የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪው ኢሰመኮ ተናግሯል