EHRC has engaged key stakeholders to resolve the issue through dialogue and prioritizing human rights
ኢሰመኮ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እና ከታገዱት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግ ለጉዳዩ መፍትሔ ለማስገኘት ሢሠራ ቆይቷል
ኢሰመኮ ባደረገው ጥረትም በአራቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ከዛሬ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ መነሳቱን አስታውቋል
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እግድ ጥሎባቸው የነበሩ አራት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የተጣለባቸው እገዳ መነሳቱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል
የአዋጁን ውጤታማ አተገባበር ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት መሥራት አለባቸው
ኢሰመኮ በሰብአዊ መብቶች ላይ ከሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በትብብርና በቅንጅት መሥራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል
በማረሚያ ቤቶች ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍና የታራሚዎችን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ለማሻሻል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብና የተቀናጀ ሥራ ይጠይቃል
States Parties shall seek lasting solutions to the problem of displacement by promoting and creating satisfactory conditions for voluntary return, local integration or relocation on a sustainable basis and in circumstances of safety and dignity
ተዋዋይ ሀገራት በዘላቂነት እና ደኅንነትንና ክብርን በጠበቀ መልኩ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የመመለስ፣ ከአካባቢ ማኅበረሰብ ጋር ተዋሕዶ የመኖር ወይም ወደ ሌላ ቦታ የማስፈር መፍትሔዎችን ለማመቻቸት አጥጋቢ የሆኑ ሁኔታዎች በማበረታታትና በመፍጠር ለመፈናቀል ችግር ዘላቂ መፍትሔዎችን ማፈላለግ አለባቸው
ኢትዮጵያ ውስጥ የጋራ የሚያስተሳስሩ እሴቶች እየተሸረሸሩ መምጣት ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ምክንያት ናቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ተናገሩ