በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን እና ምልክቶቻቸውን አስመልክቶ የባለድርሻዎችን ግንዛቤ ማሳደግ ጥቃቶቹ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ከማስከተላቸው በፊት ለመከላከል ያስችላል
ከምርጫው ጋር የተገናኙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ጥቆማዎችና አቤቱታዎች ለሰብአዊ መብቶች ክትትል ባለሙያዎች፣ በአቀራቢያ በሚገኙ የኢሰመኮ የከተማ ጽሕፈት ቤቶች በአካል በመገኘት ወይም በነጻ የስልክ መስመር 7307 ላይ በመደወል ማቅረብ ይቻላል
በሰብአዊ መብቶች መርሖችና ድንጋጌዎች የተቃኘ አያያዝ በወንጀል ነክ ነገር ውስጥ ገብተው የተገኙ ሕፃናት በመልካም ባሕሪ ታንጸው ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ አስፈላጊ ነው
ወቅታዊ እና ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳዎችን ተገንዝቦ አስተዋፆ የማድረግ ዐቅም ያለው ትውልድ በማፍራት ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ይቻላል
የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ በኢትዮጵያ "ሹማን" የተባለውን ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያዊያን የመብት ተሟጋቾች ሸለመ። ሽልማቱ የተሰጠው ዴሞክራሲን፣ የሕግ የበላይነትን፣ ሰብአዊ መብቶችን፣ መቻቻልን እና እኩልነትን በማስፋፋት ረገድ የላቀ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ለተባሉ ሰዎች ነው
በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ ቅጥር ግቢ በተካሄደ የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት (Schuman EU Awards) የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ጨምሮ ከስድስት በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሽልማቱን ማግኘት ችለዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማእከል ዋና ዳይሬክተር ያሬድ ኃይለማርያምን ጨምሮ ስምንት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ግለሰቦችና ተቋማት የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት ተበረከተላቸው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በግል ስራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች መብት ዙሪያ ከሰጠኋቸው ምክረ ሃሳቦች አብዛኞቹ አልተተገበሩም አለ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ ቅጥር ግቢ በተካሄደ የሽልማት ሥነ ሥርዓት የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት (Schuman EU Awards) ተበርክቶላቸዋል
ዛሬ በኢትዮጵያ በሚገኘው የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ ቅጥር ግቢ በተካሄደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ከተሻላሚዎቹ አንዱ የሆኑት ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ ሽልማቱ ለመላው የሥራ ባልደረቦቻቸውና ኢሰመኮን ለሚደግፉ በሙሉ አበረታች ዕውቅና የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል