The state-linked Ethiopian Human Rights Commission has also stepped into the fray, releasing a statement on Friday accusing the security forces of using excessive force against followers of the main church
ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከተከሰተው ችግር ጋር በተያያዘ የመንግሥት የፀጥታ አባላት ተመጣጣኝ ባልሆነ ኃይል በጥይት እና በድብደባ ግድያዎችን መፈጸማቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ
ኮሚሽኑ ከመደበኛው የክትትል እና የምርመራ ሥራው ጎን ለጎን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በሙሉ በማነጋገር እና በመመካከር ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና እንዲረጋገጡ የሚያስችል የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የመከላከል ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል
Female circumcision and related acts are punishable by Articles 565 and 566 of the FDRE Criminal Code
የሴት ልጅ ግርዛት እና ተያያዥ ድርጊቶች በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ፣ አንቀጽ 565 እና  አንቀጽ 566 መሠረት የሚያስቀጡ ተግባራት ናቸው
The agreement was signed by the Minister of Education, Prof. Birhanu Nega and the Chief Commissioner of EHRC, Daniel Bekele
ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ዋና ኮሚሽነር ዳኤንል በቀለ (ዶ/ር) ፈርመዋል
ስምምነቱ የሰብአዊ መብቶች እሴቶችን ወደ ማኅበረሰቡ ከማስረጽ አኳያ ተደራሽነትን በመጨመር በኢትዮጵያ ዘላቂና ውጤታማ በሆነ መንገድ የሰብአዊ መብቶች ባህልን ለማስፈን ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው
Everyone has the right to assemble and to demonstrate together with others peaceably and unarmed, and to petition
ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው