ጊዳ ኪራሙ ወረዳን ጨምሮ በተለያዩ የምስራቅ ወለጋ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በአስጊ ሁኔታ ይገኛሉ
ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. በታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት ከ150 በላይ ነዋሪዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና ሌሎች ሰዎች ለኮሚሽኑ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሀገራዊ ምርጫ 2013 ዓ.ም. ባለ6 ነጥብ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ይፋ በማድረግና ለሰብአዊ መብቶች ትኩረት እንዲሰጥ ከመወትወት በተጨማሪ፤ በቅድመ ምርጫውና በምርጫው ቀን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሲያከናውን ቆይቷል።
ክትትሉ በተከናወነባቸው የተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎችና አካባቢዎች የተመለከታቸው ክፍተቶች ተገቢው ትኩረት እንዲያገኙና አስፈላጊውን የሕግና የአተገባበር መፍትሔ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገለጸ