





የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በኅዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. የከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት አርዳ ጅላ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሕይወትና የአካል ጉዳት ስለመፈጸሙ በደረሰው ጥቆማ መሰረት፣ ከታኅሣሥ 7 እስከ ታኅሣሥ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በቦታው በመገኘት ምርመራ አካሂዷል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሀገራዊ ምርጫ 2013 ዓ.ም. ባለ6 ነጥብ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ይፋ በማድረግና ለሰብአዊ መብቶች ትኩረት እንዲሰጥ ከመወትወት በተጨማሪ፤ በቅድመ ምርጫውና በምርጫው ቀን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሲያከናውን ቆይቷል።