በሶማሊ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት በአካባቢው የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው አሳሳቢ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቅሷል
በተኩስ ልውውጡ ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች በቆሎጂ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ እንደነበሩ ኮሚሽኑ ገልጿል
በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 6 ሰዎች መገደላቸወን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ
በካምፓላ ስምምነት መሠረት የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን የመጠለያ ጣቢያዎች ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ተግባራት ሊቆጠቡ ይገባል
ኢሰመኮ አነጋገርኳቸዉ ያላቸዉ የመንግስት ባለስልጣናት የማቆያ ጣቢያዉ ዓላማ «ከየጎዳናዉ የተነሱት ሰዎች በመልሶ ማቋቋም መርሐ-ግብር መሠረት ወደየመጡበት እንዲመለሱ ለማገዝ ነዉ» ማለታቸዉን ኮሚሽኑ ጠቅሷል
የጎዳና ተዳዳሪዎችን በግዳጅ ማቆያ ማዕከላት እንዲገቡ የማድረግ ተግባር በአፋጣኝ እንዲቆምና ለዚሁ ለችግር ዘለቄታዊና ሁሉን አቀፍ የፖሊሲ ምላሽ እንዲሰጥ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ
ይህን ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአስገዳጅ ሁኔታ ከጎዳና ላይ እያፈሱ ወደ ሌላ ቦታ የመውሰዱ አሰራር በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስቧል
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ጊዜያዊ የሰዎች ማቆያ ስፍራ በተላላፊ በሽታ ምክንያት የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። የኦሮሚያ ክልል በበኩሉ በክልሉ የሰዎች ማቆያ ስፍራ አለመኖሩን ይገልጻል
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ በሚገኝ ጊዜያዊ ማቆያ ማዕከል ውስጥ ተላላፊ በሽታ ተከስቶ የ3 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
በማቆያ ማእከሉ እንዲገቡ ስለሚደረጉ ሰዎች አያያዝ እና ስለ ግዳጅ አሠራሩ ኢሰመኮ ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ክትትል እና ውትወታ በማድረግ የሰጣቸውን ምክረ ሐሳቦች በማስታወስ፣ ይህንን የግዳጅ አሠራር በአፋጣኝ ከማስቆም በተጨማሪ ለችግሩ ዘለቄታዊ እና ሁሉን አቀፍ የፖሊሲ ምላሽ ይሻል