የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በኅዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዳማ ኦሊያድ ሲኒማ፣ በኅዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ደግሞ በሀዋሳ ከተማ ሌዊ ሲኒማ በመጨረሻም በታኅሣሥ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በጋርደን ግሩቭ ዎክ መናፈሻ ይካሄዳል
ስልጠናው ወጣቶች በሰላም በጋራ መኖርን እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ካሉ ልዩነቶችን መሰረት አድርገው የሚከሰቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመከላከል ሥራ ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የማስቻል አላማ ያለው ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሀገራዊ ምርጫ 2013 ዓ.ም. ባለ6 ነጥብ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ይፋ በማድረግና ለሰብአዊ መብቶች ትኩረት እንዲሰጥ ከመወትወት በተጨማሪ፤ በቅድመ ምርጫውና በምርጫው ቀን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሲያከናውን ቆይቷል።
ክትትሉ በተከናወነባቸው የተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎችና አካባቢዎች የተመለከታቸው ክፍተቶች ተገቢው ትኩረት እንዲያገኙና አስፈላጊውን የሕግና የአተገባበር መፍትሔ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገለጸ