አባል ሀገራት የእርስ በርስ ድጋፍን በመጠቀም ጭምር አካል ጉዳተኞች የላቀ ነጻነት፣ የተሟላ አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ ማኅበራዊና ሞያዊ ችሎታ እንዲሁም በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ውስጥ የተሟላ ተካታችነትና ተሳትፎ እንዲኖራቸው እና ይህንንም አስጠብቀው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ውጤታማና ተገቢ እርምጃዎችን ይወስዳሉ
EHRC Participated in a side event on the Rights of Persons with Disabilities hosted by Global Alliance of National Human Rights Institutions (GANHRI) in Geneva
የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የትምህርት መብት ለማረጋገጥ የመምህራንን ግንዛቤ በማዳበር የትምህርት አሰጣጡ ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ እንዲሆን ማስቻል ይገባል
ዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት በሀገራዊ ቋንቋዎች መተርጎም የስምምነቱን ተደራሽነት በማስፋት ለአካል ጉዳተኞች ሰብአዊ መብቶች መከበር አስተዋጽዖ አለው
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፀጥታ ጥበቃና ከገጽታ ግንባታ ጋር በተያያዘ ምክንያት የንግድ ቦታቸው የፈረሰባቸው አካል ጉዳተኞች፣ ለልመና ወደ አደባባይ መውጣታቸውን፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) has urged the government to address the urgent needs of people with disabilities who have lost their business establishments due to there recent wave of demolitions in the city. This appeal follows the 2023 dismantling of small trading businesses by the city administration, which has left many disabled business owners without their means of livelihood
አባል ሀገራት ለአካል ጉዳተኞች ትምህርት የማግኘት መብት ዕውቅና ይሰጣሉ
States Parties recognize the right of persons with disabilities to education
ሠራተኞች በሥራ ላይ በሚደርስ አደጋ ወይም በሥራ ምክንያት በሚመጣ በሽታ ለአካል ጉዳት ይዳረጋሉ። የአካል ጉዳት የመሥራት ችሎታ መቀነስን ወይም ማጣትን በሚያስከትል ሁኔታ በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳት ሲሆን፣ ጊዜያዊ የአካል ጉዳት፣ ዘላቂ ከፊል የአካል ጉዳት፣ ዘላቂ ሙሉ የአካል ጉዳት ወይም ሞት ሊያስከትል ይችላል
የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተደራሽ መሆን ለአካል ጉዳተኞች ሰብአዊ መብቶች መከበር እና መጠበቅ ከፍተኛ ሚና አለው