የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት የአካል ጉዳተኞችን እና የአረጋውያንን ሰብአዊ መብቶች እንዲያስከብርና ፍላጎቶቻቸውን እንዲያሟላ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይጠይቃል
ማእከላቱ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መመዘኛዎች፣ የተ.መ.ድ. የአረጋውያን መርሆችና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣውን አነስተኛ መስፈርት በማሟላት የአገልግሎቶቻቸውን ጥራት ለማሻሻል እና ዘላቂነታቸውን ለማረጋገጥ መንግሥት ድጋፍ በማድረግ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል
አባል ሀገራት አረጋውያን በሁሉም ጊዜ ሰብአዊ እንክብካቤ፣ ጥበቃ እና ክብር እንዲያገኙ የማድረግ እና የሚያስፈልጋቸውን የሕክምና ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዳይነፈጋቸው የማድረግ ግዴታ አለባቸው
States Parties shall ensure that older persons receive humane treatment, protection and respect at all times and are not left without needed medical assistance and care
ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን እንዲሁም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ከነበራቸው ተሳትፎ፣ ተደራሽነት እና አካታችነት አንጻር የተስተዋሉ ክፍተቶችን መለየት ለቀጠይ ምርጫ መሻሻል መሰረት ነው
አረጋውያንን መንከባከብ ለማእከላቱ ብቻ የሚተው ሥራ ሳይሆን በዋናነት የመንግሥት ቀጥሎም የሁሉም ማኅበረሰብ ኃላፊነት በመሆኑ፤ ችሮታ ሳይሆን የአረጋውያን እንክብካቤ የማግኘት መብት ነው