ዜጎችን ከመደበኛ የመኖሪያ ቦታቸው ያፈናቀሉ፣ የሰው ሕይወት ያጠፉ፣ ሀብት ያወደሙ፣ አካላዊ ጉዳት ያደረሱ ቡድኖችና ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ በቂ ዕርምጃዎች ባለመወሰዳቸው የሕግ በላይነት፣ ተጠያቂነትንና የተፈናቃዮችን ፍትሕ የማግኘት መብት የሚነፍግ ነው ሲል፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
ይህ ሁለተኛው የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት ኮሚሽኑ የተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ ሁኔታዎችንና ምክረ ሐሳቦችን አካቷል
ለጋሾች ለስደተኞች የጀመሩት ርዳታ በሦስተኛ ወገን እንደሚታደል ኢትዮጵያ አስታወቀች
መንግሥት ለተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ የሚሰጥና የሚያስተባብር በግልጽ ሥልጣን የተሰጠው ተቋም በማቋቋም ወደ ሥራ ማስገባት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው
ሕይወት፣ ትርጉም ያለው ሕይወት፣ ምንድን ነው? የአንድ ኢትዮጵያዊት ሴት፣ ወይም የአካል ጉዳተኛ ወይም የተፈናቃይ ወይም የአረጋዊ ሕይወት ምን ይመስላል?
ዲጂታል ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት የጎላ አስተዋጽዖ አለው
የውይይቱ ተሳታፊዎች ፍትሕ ሚኒስቴር ያወጣው ነጻ የሕግ ድጋፍ ስትራቴጂ በመጽደቁ በኢሰመኮ አስተባባሪነት እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ከስትራቴጂው ትግበራ ጋር ሊቀናጁ እንደሚገባ አስገንዘበዋል
በምግብ ሥርዓት ውስጥ ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ አቀራረብ (human rights-based approach) መከተል ያስፈልጋል
State parties shall take all appropriate measures to ensure that persons with disabilities can exercise the right to freedom of expression and opinion, including the freedom to seek, receive and impart information and ideas on an equal basis with others and through all forms of communication of their choice
አባል ሀገራት አካል ጉዳተኞች በመረጧቸው የመገናኛ ዘዴ ዐይነቶች ሁሉ መረጃን የመፈለግ፣ የመቀበል እና የማሰራጨት ነጻነትን ጨምሮ ከሌሎች ጋር በእኩልነት ሐሳብን በነጻነት የመያዝ እና የመግለጽ መብቶቻቸውን መጠቀም እንዲችሉ ተገቢውን ሁሉ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል