የአስገድዶ መሰወር ወንጀልን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ፤ ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የተደረገውን ዓለም አቀፍ ስምምነት (International Convention for the Protection of All Persons from Enforced Disappearance) ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ተቀብላ ልታጸድቅ ይገባል
በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት የሚያልፉ ሕፃናትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝና ጥበቃ ለማሻሻል ሁሉን አቀፍ ቅንጅታዊ አሠራር ያስፈልጋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኮሚሽኑ አበረታች ስራዎችን ቢሰራም፤ አልፎ አልፎ በዜጎች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን ገልጸዋል
ለችግሩ እልባት የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የምዝገባ አገልግሎት እና የመታወቂያ ሰነድ እድሳት በአፋጣኝ መጀመር አለበት
ኮሚሽኑ የሚያቀርባቸው ምክረ ሐሳቦች በመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ተግባራዊነታቸው እንዲረጋገጥ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል
በባሕርይ እና በማኅበራዊ ለውጥ ዙሪያ የሚሠሩ አካላት ብዝኃነትን ማዕከል በማድረግ የአረጋውያንን እና የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ መብቶች በማስፋፋት ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው
የአተገባበር ክትትል በተሠራበት በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና በሶማሌ ክልል የተለዩ ቦታዎች ዝናብ መዝነቡ የድርቁ አደጋ ማብቂያ ተደርጎ መወሰድ የለበትም
በሀገር ውስጥ በሰዎች የመነገድ ተግባር በተለይም በሴቶችና ሕፃናት መነገድ ሰፊና ውስብስብ ችግር በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሻል
ኮሚሽኑ በአወጣው መግለጫ፣ በከተማዋ፣ የአደባባይ በዓላት ሲከበሩ እና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች በሚኖሩበት ጊዜ፣ የጎዳና ላይ ሕፃናት ከየቦታው ያለፈቃዳቸው እየተሰበሰቡ በጅምላ ተይዘው ወደ ማቆያ ሥፍራ ይወሰዳሉ፤ ብሏል
ማንኛውም ሰው ብቻውንም ሆነ ከሌሎች ጋር በመተባበር የንብረት ባለቤት የመሆን መብት አለው