ታኅሣሥ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ፣ በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በተካሄደ ዝግጅት፣ “ተመለሽ” የተሰኘ አጭር ተውኔት እና ከመስከረም ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች በተካሄዱ ውድድሮች አሸናፊዎችን በመሸለም የተመረቀው 4ተኛው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል እስከያዝነው ወር መጨረሻ በ8 ክልል ከተሞች ይካሄዳል
በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) መሠረት የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ዕጩዎች ጥቆማ እስከ ታኅሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚቆይ ነው
መንግሥት የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች የማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ሀብት ይመድባል
The State has the obligation to allocate ever increasing resources to provide to the public health, education and other social services
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በግዳጅ የመከላከያ ሰራዊት አባል እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ብሏል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን
ኮሚሽኑ ከኅዳር 4 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ እና ሻሸመኔ ከተሞች እንዳካሄደ በገለጸው ክትትል እና ምርመራ፣ "የመከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ" በሚል ሕፃናትንና የአእምሮ ህሙማንን ጨምሮ የክልሉ ነዋሪዎች በግዳጅ መያዛቸውን አመልክቷል
ኢሰመኮ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የክልሉ አስተዳደር እና የፀጥታ አካላት ለመከላከያ ሰራዊት ምልመላ እናካሂዳለን በሚል ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን በግዳጅ እንደያዙ እንዲሁም የተያዙትን ለመልቀቅ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስገደዳቸውን ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ወደ ምርመራ ገብቻለሁ ብሏል
ኮሚሽኑ ምርመራውን በኦሮሚያ ክልል በአዳማ፣ በቢሾፍቱ፣ በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ እጩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማቆያ ስፍራዎችን በመጎብኘት፤ በማቆያ ስፍራዎቹ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን በጉዳዩ ዙሪያ ቃለ መጠይቅ ማድረጉን ገልጿል
ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን ከሕግ ውጪ የያዙ እና ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገደዱ የክልሉ መንግሥት የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት ላይ የተሟላ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል
የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች መከበር እና መጠበቅ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል