በሀገሪቱ በተከሰቱ ሰው ሠራሽ ቀውሶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች ሳቢያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶችና ሕፃናትን ለመፈናቀል፣ ለጾታዊ ጥቃቶች እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲሁም ለሌሎች ተደራራቢ የመብት ጥሰቶች ተጋላጭነታቸውን እንደጨመረ በሪፖርቱ ገልጿል
በሕግ፣ በፖሊሲና በአሠራር ረገድ የኮሚሽኑን ምክረ ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ ለሴቶች እና ለሕፃናት መብቶች የተሻለ ጥበቃ ማድረግ ይገባል
ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት በተለይ የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ኮሚሽኑ የለያቸውን አበረታች እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን እና ምክረ-ሐሳቦችን አካቷል