ከአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታው ጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት በተጨማሪ የፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ ወቅት ክትትል (Parliamentary Oversight) እና የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትል የማድረግ ኃላፊነት ሊረጋገጥ ይገባል
Everyone has the right to seek and enjoy in other countries asylum from persecution
ማንም ሰው ከጥቃት ለማምለጥና በሌሎች ሀገራት ጥገኛ ሆኖ ለመኖር የመጠየቅ መብት አለው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እየተባባሰ የመጣውን የትጥቅ ግጭት እና የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም አማራጭ ቅድሚያ እንዲሰጠው ጠይቋል
የሕግ አስከባሪ ተቋማት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁንና ደንቡን በሥራ ላይ ሲያውሉ እና ሲያስፈጽሙ ከዚህ በታች በተመለከቱት የሰብአዊ መብቶች እና ሕገ መንግሥታዊ መርሖች እንዲመሩ፣ በማናቸውም ሁኔታ ሊገደቡ የማይችሉ መሠረታዊ መብቶችን እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ፣ እንዲሁም በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና የሙያ ሥነ ምግባር እንዲመሩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በከፍተኛ አደራ ጭምር እያሳሰበ አፈጻጸሙንም በስልታዊ መንገድ የሚከታተል መሆኑን ይገልጻል፡፡  
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የተቀበሩና የወዳደቁ ፈንጂዎች በአፋር ክልል 27 ሰዎችን፣ በአማራ ክልል ቁጥራቸው ያልተገለፀ ሰዎችን ለሞት እንዲሁም ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
በሰው የመነገድ ወንጀል ማለት ግለሰቦችን ለብዝበዛ በማስገደድ፣ በመጥለፍ፣ በማታለል ወይም በኃይል በመመልመል፣ በማጓጓዝ፣ በማሸጋገር፣ በመቀበል፣ ወይም በማስጠለል የሚፈጸም ድርጊት ነው
Every individual shall have the right to have his cause heard
ማንም ሰው በደሉ እንዲሰማለት የማድረግ መብት አለው
በሰው የመነገድ ወንጀል ሰለባ የሆኑ ሰዎች ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮ የተሟላ ድጋፍ እና ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ