ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነውና ለሦስተኛ በጀት ዓመት ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዓመታዊ ሪፖርት ያካተታቸው አንኳር ጉዳዮች። ሙሉ ሪፖርቱ እዚህ ተያይዟል The full report is linked here (English) Executive Summary for the report (English)
ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነውና ለሦስተኛ በጀት ዓመት በዚህ መልኩ ተጠናቅሮ ይፋ የተደረገው ይህ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዓመታዊ ሪፖርት ኮሚሽኑ ባደራጃቸው ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች እና የከተማ ጽሕፈት ቤቶች አማካኝነት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ጠቅለል ባለ መልኩ የሚዳስስ ነው። The full report is...
ኢሰመኮ ይህን ያለው ሰኔ 16/2016 ዓ.ም በ4 ክልሎች የተካሄደውን የ6ኛ ዙር ቀሪና ድጋሚ ምርጫ የሰብአዊ መብቶችን ክትትል በመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ነው
ሰኔ 21፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሰኔ 16 ቀን በተካሄደው የ6ኛው የቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ወቅት የነበሩ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ክትትል የያዘ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ አድርጓል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ትላንት ማክሰኞ የጸደቀው፣ የመሬት ይዞታ ካሳ ክፍያ የዐዋጅ ማሻሻያ፣ የመብት ጥሰትን ያስከትላል፤ ሲል ተችቷል
በትጥቅ ግጭት ውስጥ በሚገኘው የዐማራ ክልል ርእሰ መዲና ባሕር ዳር ከተማ፣ ላለፉት ሁለት ቀናት የተካሔደውን የሰላም ጉባኤ የተሳተፉ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ በግጭቱ ዐውድ ውስጥ የታሰሩ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች እና ተጽእኖ ፈጣሪ ዜጎች እንዲፈቱ ጠይቀዋል
እያንዳንዱ አባል ሀገር በሕግ ሥርዓቱ ውስጥ የማሰቃየት ተግባር ሰለባ የሆነ ሰው መፍትሔ እንደሚያገኝ እንዲሁም በተቻለ መጠን የተሟላ ማገገሚያን ጨምሮ ተፈጻሚነት ያለው ፍትሐዊና በቂ ካሳ የማግኘት መብት እንዳለው ማረጋገጥ አለበት
Each State Party shall ensure in its legal system that the victim of an act of torture obtains redress and has an enforceable right to fair and adequate compensation, including the means for as full rehabilitation as possible
ከምርጫው ጋር የተገናኙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ጥቆማዎችና አቤቱታዎች ለሰብአዊ መብቶች ክትትል ባለሙያዎች፣ በአቀራቢያ በሚገኙ የኢሰመኮ የከተማ ጽሕፈት ቤቶች በአካል በመገኘት ወይም በነጻ የስልክ መስመር 7307 ላይ በመደወል ማቅረብ ይቻላል
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም፣ በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሠረተ ልዩነት ሳይደረግበት በማናቸውም የመንግሥት ደረጃ በየጊዜው በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥ እና የመመረጥ መብት አለው