በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዘጋጅነት ለ3ኛ ጊዜ የሚካሄደው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በኢሰመኮ የ2015 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ በመሆን ከተለዩት መብቶች መካከል በሕይወት የመኖር መብት እና በቂ የሆነ መኖሪያ ቦታ/ቤት የማግኘት መብት ዙሪያ የሚያተኩር ይሆናል። በኢሰመኮ አዘጋጅነት ለሚካሄደው 3ኛ ዙር ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የሚቀርቡ የኪነጥበብ ሥራዎች...
የ2016 ዓ.ም. የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በሕይወት የመኖር መብት እና በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ ኅዳር 30 ቀን የሚውለው የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች መግለጫ 75ኛ ዓመት የሚታሰብበት ዝግጅት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፤ ሁሉም ሰው በውድድሩ እንዲሳተፍ እና ሂደቱን እንዲከታተል ተጋብዟል
በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 6 ሰዎች መገደላቸወን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ
የመሬት ይዞታን ለልማት/ለሕዝብ ጥቅም/ ማስለቀቅ እና የሰብአዊ መብቶች መርሆች ቅድመ ማስለቀቅ፣ በማስለቀቅ ወቅት እንዲሁም ድኅረ ማስለቀቅ ጊዜ መንግሥት ሊያሟላ የሚገባቸው የሰብአዊ መብቶች መርሆችን ያልተከተለ ሲሆን በኃይል ማፈናቀል እንደተፈጸመ ይቆጠራል፡፡ ይዞታ የማስለቀቅ ተግባር በአጠቃላይ ሰዎችን ቤት አልባ እንዲሆኑ እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጋላጭ ማድረግ የለበትም፡፡
በአማራ ክልል ለወራት በቀጠለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት ድሮንን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች በተሰነዘሩ ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ
በቂ መኖሪያ የማግኘት መብት (አንቀጽ 11/1)፡ በኃይል ማፈናቀል 20/05/97 የኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ኮሚቴ አጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 7 (አጠቃላይ ትንታኔዎች) የቃልኪዳን ስምምነቱ ምህጻረ ቃል፡- 1 ሲኢኤሲአር አጠቃላይ ትንታኔ 7 በቂ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት (የቃል ኪዳኑ አንቀጽ 11/1)፡ በኃይል ማፈናቀል
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ ) የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ አጠቃላይ አስተያየት ቁጥር 36 በሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን አንቀጽ 6፦ በሕይወት የመኖር መብት
የክልል ምክር ቤቶችን የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ቁጥጥር ዐቅም ማጎልበት ለሰብአዊ መብቶች መከበርና መስፋፋት ከፍተኛ ሚና አለው
ኮሚሽኑ በቅርብ ጊዜ አደርግሁት ባለው ክትትል "በስደተኞች ሠፈሮች ውስጥ የከፋ ሰብአዊ ሁኔታ እና የምግብ አቅርቦት እጥረት እየጨመረ መምጣቱን አሳሳቢ ብሎታል። የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የርዳታ ድርጅቶች ለስደተኞች ይሰጡት የነበረዉን ሰብአዊ ርዳታ ማቋረጣቸዉን አስታዉቋል
“በሌሎችም የአገሪቱ አካባቢዎች ለከፋ ረኀብ ተጋልጠዋል” - ኢሰመኮ