Every human being has the inherent right to life. This right shall be protected by law. No one shall be arbitrarily deprived of his life
ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነውና ለአራተኛ በጀት ዓመት በዚህ መልኩ ተጠናቅሮ ይፋ የተደረገው ይህ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዓመታዊ ሪፖርት ኮሚሽኑ ባደራጃቸው ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች እና የከተማ ጽሕፈት ቤቶች አማካኝነት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ጠቅለል ባለ መልኩ የሚዳስስ ነው። የሪፖርቱ አንኳር ጉዳዮች Executive...
ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች በእኩልነት የሚያሳትፍ እና አካታች የሀገራዊ ምክክር፤ በሰብአዊ መብቶች መርሖች ላይ የተመሠረተ እና ተጎጂዎችን ማእከል ያደረገ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራን ማረጋገጥ ይገባል
ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነውና ለአራተኛ በጀት ዓመት ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዓመታዊ ሪፖርት ያካተታቸው አንኳር ጉዳዮች በእንግሊዝኛ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (Click here for the English version) ሙሉ ሪፖርቱ እዚህ ተያይዟል
ለማንኛውም ዓላማ በሰው የመነገድ ተግባር የተከለከለ ነው
Trafficking in human beings for whatever purpose is prohibited
በሰብአዊ መብቶች ላይ በጋራ መምከር እና አጋርነትን ማጠናከር ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበር እና ጥበቃ ጉልህ ሚና አለው
ኮሚሽነሮቹ በሰጡት አመራር የኢሰመኮን ሥራ በማጠናከር፣ ተደራሽነቱን በማስፋት እና በሕዝብ እንዲሁም በዓለም አቀፍ አጋሮች ዘንድ መተማመንን በማሳደግ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሚና አበርክተዋል
በሰብአዊ መብቶችና በሲቪክ ምኅዳሩ ዙሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚታዩ ተግዳሮቶች መፍትሔ ለማምጣት የሚመለከታቸው አካላት በአጋርነት ሊሠሩ ይገባል
እያንዳንዱ አባል ሀገር በሕግ ሥርዓቱ ውስጥ የማሠቃየት ተግባር ሰለባ የሆነ ሰው መፍትሔ እንደሚያገኝ እንዲሁም በተቻለ መጠን የተሟላ ማገገሚያን ጨምሮ ተፈጻሚነት ያለው ፍትሐዊና በቂ ካሳ የማግኘት መብት እንዳለው ማረጋገጥ አለበት