ኮሚሽኑ ዓላማውን ለማስፈጸም ከሚሰራቸው ሰብአዊ መብቶችን የማስተማር እና የማስፋፋት ስራ ውጤታማ እንዲሆን ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በአጋርነት የሚሰራ ሲሆን፣ ከሀገራዊ የኪነጥበብና የሥነ ጥበብ ባለሞያዎችና ማኅበራት ጋር የሚያደርገውን ትብብር በተመሳሳይ መልኩ እኩል ክብደት የሚሰጠው ነው
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2030 ደኅንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና አጠባበቅ አቅርቦትን ለሁሉም የማረጋገጥ እቅድ ይዛለች። (ዘላቂ የልማት ግብ 6)
ለባለፉት በርካታ ወራት ሰፊ አካታች ሂደት ሲዘጋጅ የቆየው ይህ የስትራቴጂ እቅድ ኮሚሽኑ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሊሰሩና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሎ የለያቸው ቁልፍ የውጤት መስኮችንና ዋና ዋና ተግባራትን አካቷል።