በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ቁጥር 39/46 አባል ሀገራት እንዲፈርሙበት እና እንዲያጸድቁት ክፍት የተደረገ በሥራ ላይ የዋለበት ጊዜ ሰኔ 26 ቀን 1987 እ.ኤ.አ.
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር በተፈጥሯዊ የሰው ልጅ ክብርና እኩልነት መርሆዎች መመስረቱን፤ እንዲሁም ሁሉም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገራት ድርጅቱ የተመሰረተበት ዓላማ፤ ማለትም ምንም ዓይነት የዘር፣ የቀለም፣ የጾታ፣ የቋንቋ ወይም የሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግ የማንኛውም ሰው ሰብአዊ መብቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስከበርና ለማጋገጥ ከድርጅቱ ጋር በመተባበር በግልና በጋራ እርምጃ ለመውሰድ የገቡትን ቃል ኪዳን ግምት ውስጥ...
Adopted and opened for signature and ratification by General Assembly resolution 2106 (XX) of 21 December 1965 entry into force 4 January 1969, in accordance with Article 19

ይህ ቻርተር ከአሕጉራችን የሰብአዊ መብት ሰነዶች ቀዳሚው ነው፡፡ ይህን ቻርተር ፈርመው የተቀበሉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል ሀገራት በዚህ ቻርተር የተደነገጉትን መብቶች፣ ግዴታዎችና ነጻነቶች አውቀው በመቀበል ለተግባራዊነታቸው ሕግ ለማውጣትና ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድ ግዴታ ገብተዋል፡፡
የአፍሪካ ሕፃናት መብቶችና ደኅንነት ቻርተር፡፡ የቻርተሩ ተዋዋይ ሀገራት የሆኑ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል ሀገራት በቻርተሩ ለተደነገጉ መብቶች፣ ነጻነቶችና ግዴታዎች ዕውቅና የመስጠት የቻርተሩ ድንጋጌዎችን ተፈጻሚ ለማድረግ በቻርተሩና በየሕገ-መንግሥቶቻቸው በተመለከቱ ድንጋጌዎች መሰረት እንደ አስፈላጊነቱ የሕግ ማውጣትን እና ሌሎች እርምጃዎች የመውሰድ ግዴታ አለባቸው፡፡



