የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመንግስት የቀረበለትን ውሳኔ ሃሳብ በአፋጣኝ እንደሚያጸድቀው ኮሚሽኑ ተስፋውን እየገለጸ፤ የመንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ አሁንም በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጥሪውን ያቀርባል
ከእስር ከተለቀቁት መካከል ሴቶች፣ አረጋውያን፣ የጤና ችግር ያለባቸው እና ሌሎች ጉዳያቸው ተጣርቶ በቀላል ዋስትና የተለቀቁ ሰዎች ይገኙበታል
ለባለፉት በርካታ ወራት ሰፊ አካታች ሂደት ሲዘጋጅ የቆየው ይህ የስትራቴጂ እቅድ ኮሚሽኑ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሊሰሩና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሎ የለያቸው ቁልፍ የውጤት መስኮችንና ዋና ዋና ተግባራትን አካቷል።
በአጠቃላይ ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል ለማረጋገጥ እንደቻለው ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መተግበር ባለበት መንገድ በተለይም “የጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነፃ መሆን” የሚሉትን የሰብአዊ መብት መርሆዎችን ባከበረ መልኩ አለመተግበሩን ተመልክቷል።
ሪፖርቱ በአገር ውስጥም በዓለም አቀፍ ደረጃም ጥሩ ምላሽና ተቀባይነት አግኝቷል ብዬ አምናለሁ።
የተፈጸሙ ጥሰቶች የጦር ወንጀል ስለመሆናቸው አመላካች ሁኔታዎች አሉ
በጦርነቱ ወቅት ትግራይ ውስጥ “ተፈጽመዋል” የተባሉት የሰብዓዊ መብት ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን፣ የስብዕና እና የስደተኛ ሕግጋት መጣስ ሲያጣራ የቆየው ጥምር መርማሪ ቡድን ባወጣው የግኝቱ ሪፖርት የጦር ወንጀሎች እና በስብዕና ላይ የተፈጸሙ ሊባሉ የሚችሉ ወንጀሎች በሁሉም ወገኖች ስለመፈጸማቸው አሳማኝ መሰረቶች አሉ ብሏል።
ኢሰመኮ ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ባደረገው ውይይት የታሳሪዎችን ደህንነት ስለማረጋገጥ መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ላይ ተመካክሯል
ጊዳ ኪራሙ ወረዳን ጨምሮ በተለያዩ የምስራቅ ወለጋ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በአስጊ ሁኔታ ይገኛሉ