የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 1(በ)፣ 4(2)(ለ) እና 11(1)
- አባል ሀገራት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ሁሉም ዐይነት ጥቃቶችን የሚከለክሉ ሕጎችን ለማውጣት እና ለማስፈጸም ተገቢ እና ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው። በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት በሰላም ጊዜ እንዲሁም በትጥቅ ግጭት ወይም ጦርነት ጊዜ የሚፈጸሙ የጥቃት ድርጊቶችን ያጠቃልላል።
- አባል ሀገራት በሕዝብ በተለይም በሴቶች ላይ ተጽዕኖ በሚያደርሱ የትጥቅ ግጭት ሁኔታዎች ውስጥ ተፈጻሚነት ያላቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ደንቦች የማክበር እና የማስከበር ግዴታ አለባቸው።