ቤተሰብ የሕብረተሰብ የተፈጥሮ መሠረታዊ መነሻ ነው። ከሕብረተሰብና ከመንግሥት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው።
(የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፋዊ መግለጫ፣ አንቀጽ 16)
በሕግ በተወሰነው የጋብቻ ዕድሜ የደረሱ ወንዶችና ሴቶች፤ ዘርን፣ ብሔርን፣ ብሔረሰብን ወይም ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግባቸው የማግባት እና ቤተሰብ የመመሥረት መብት አላቸው።
በጋብቻ አፈጻጸም ፣ በጋብቻ ዘመንና በፍቺ ጊዜ እኩል መብት አላቸው ።
(የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 34)