የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 40(2)
የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ጥሷል የተባለ ወይም በመጣሱ የተከሰሰ ማንኛውም ሕፃን ከሚኖሩት ዋስትናዎች መሃከል፡-
- በሕግ መሠረት ጥፋተኛነቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ንጹሕ ሆኖ የመገመት፤
- የቀረበበትን ክስ በፍጥነትና በቀጥታ፣ አስፈላጊ ሲሆንም በወላጆቹ ወይም በሕጋዊ አሳዳሪዎቹ በኩል የማወቅ፤ እንዲሁም ለክሱ መከላከያ አዘጋጅቶ ለማቅረብ የሕግ ወይም አግባብነት ያለው ሌላ ዕርዳታ የማግኘት፤
- የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉን ጥሷል ተብሎ ከተፈረደበት ይህ ፍርድና በፍርዱ መሠረት የተወሰዱት እርምጃዎች ሁሉ ሥልጣን ባለውና ነጻና ገለልተኛ በሆነ የበላይ ባለሥልጣን ወይም የዳኝነት አካል በሕግ መሠረት እንዲመረመርለት ማድረግ ይገኙበታል፡፡
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 36(3)
ወጣት አጥፊዎች በማረሚያ ወይም በመቋቋሚያ ተቋሞች ከአዋቂዎች ተለይተው መያዝ አለባቸው፡፡