የአፍሪካ ወጣቶች ቻርተር፣ አንቀጽ 14 (1) እና (2(ለ – መ))
- አባል ሀገራት ለወጣቶች ሁለንተናዊ እድገትን የሚያረጋግጥ በቂ የሆነ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት ዕውቅና ሊሰጡ ይገባል።
- አባል ሀገራት የወጣቶችን ከረሃብ ነጻ የመሆን መብት በመገንዘብ የተናጠል ወይም የጋራ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል፡፡ ይህም፡-
• ወጣቶች ዘመናዊ አሠራርን በመጠቀም የግብርና፣ የማዕድን፣ የንግድ እና የኢንዱስትሪ ምርት እንዲማሩ ማሰልጠን እና የዘመናዊ የመረጃና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ጥቅሞችን በማስተዋወቅ ነባርና አዳዲስ ገበያዎችን እንዲያገኙ ማድረግ፤
• ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት የሚውል የመሬት ስጦታ ለወጣቶች እና ለወጣት አደረጃጀቶች ማበርከት፤ እና
• የወጣቶችን ተሳትፎ በግብርና እና ሌሎች ዘላቂ መተዳደሪያ ፕሮጀክቶች ለማበረታታት የብድር አቅርቦት ማመቻቸትን ያካትታል፡፡