የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 29 

  • ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው።
  • የፕሬስ እና የሌሎች መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም የሥነ ጥበብ ፈጠራ ነጻነት ተረጋግጧል።
  • የፕሬስ ነጻነት በተለይ የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑን እና የሕዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት ዕድልን ያካትታል።

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2021፣ አንቀጽ 86(1) 

በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በዐቃቢ ሕግ አማካኝነት ለፍርድ ቤት መቅረብ አለበት።