© UNICEF Ethiopia 2020 Mulugeta Ayene

በግጭት/በጦርነት ወቅት የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን የሚመለከቱ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ማዕቀፎች አሉ። በእነዚህ ማዕቀፎች ከተጠቀሱ ተግባራት መካከል በሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶች ላይ የተቀናጀና ወቅታዊ መረጃዎች ማሰባሰብ፣ ጥቃቶችን ለመከላከልና ተጠያቂነት ለማስፈን በጊዜ ገደብ የተለዩና ተጨባጭ እርምጃዎች መውሰድ እና በተጎዱ አካባቢዎች የሚቀርቡ ሰብአዊ እርዳታዎች በአስገድዶ መደፈር የሚከሰት እርግዝናን ጨምሮ የተሟላ የሴቶች የወሊድ ጤና ክትትል አገልግሎት እንዲያካትቱ የሚመክሩት ይገኙበታል።