በማንኛውም ሰው የግል ሕይወት፣ ቤተሰብ፣ መኖሪያ ቤት ወይም ደብዳቤ ላይ ያለ አግባብ ወይም ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ጣልቃ ገብነት አይፈጸምም፡፡ መልካም ዝናውም ከሕግ ውጭ አይደፈርም፡፡ (የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ስምምነት፣ አንቀጽ 17(1))
መረጃን የሚሰበስቡ፣ የሚያከማቹ፣ የሚጠቀሙ እና የሚያጋሩ የንግድ ድርጅቶች (የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ጨምሮ) ከሥራቸው ጋር ተያይዞ በሰብአዊ መብቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመለየት፣ ለመከላከል፣ ለማቃለል እና ለማስተካከል የሰብአዊ መብቶችን መሰረት ያደረጉ እርምጃዎችን ለመውሰድ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡ (ተ.መ.ድ የንግድና ሰብአዊ መብቶች መመሪያ መርሆች II. B. 17)