የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 19 (ሀ) (ሐ)
ሴቶች ዘላቂ ልማት የማግኘት መብታቸውን ሙሉ በሙሉ የመጠቀም መብት አላቸው። አባል ሀገራት፦
- በብሔራዊ የልማት ዕቅድ ሂደቶች ውስጥ ሥርዓተ ጾታን ለማካተት፤
- እንደ መሬት ያሉ ምርታማ ሀብቶች ላይ የሴቶችን ተደራሽነት እና ቁጥጥር ለማሳደግ እንዲሁም የንብረት መብትን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ መውሰድ አለባቸው።
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 35 (6)
ሴቶች በብሔራዊ የልማት ፖሊሲዎች ዕቅድና በፕሮጀክቶች ዝግጅትና አፈጻጸም፣ በተለይ የሴቶችን ጥቅም በሚነኩ ፕሮጀክቶች ላይ ሐሳባቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲሰጡ የመጠየቅ መብት አላቸው።