የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) 2024–2028 የ“ባስኬት ፈንድ” ፕሮጀክት የማስተባበሪያ ኮሚቴ (Steering Committee) መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።





በአዲስ አበባ በሚገኘው የኢሰመኮ ዋና መሥሪያ ቤት እና በበይነ መረብ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎን ጨምሮ ሁሉም ኮሚሽነሮች እንዲሁም የኮሚሽኑ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ተወካዮች እና የባስኬት ፈንድ ለጋሽ ሀገራት አባላት ተወካዬች ተሳትፈዋል።
በስብሰባው ላይ የሰብአዊ መብት ሥራዎች እንዲጠናከሩ እና የፕሮጀክቱ አፈጻጸም የተሻለ እንዲሆን የተሰሩ ሥራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።



በውይይቱ በሀገሪቱ ያሉ ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ እና በፕሮጀክቱ ሂደት ላይ ያላቸው ተጽዕኖ የተገመገመ ሲሆን፣ ከጥር እስከ ሐምሌ 2026 የሥራ አፈጻጸም እና የፋይናንስ ሪፖርቶች ቀርበዋል።
በውይይቱ ወቅት ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የሰብአዊ መብቶችን በማስፋፋት በማስከበር ረገድ ኮሚሽኑ ትልልቅ ስኬቶች ማስመዝገቡን ገልፀው ፣ ለእነዚህ ስኬቶች መመዝገብ የዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ተቋም እና የባስኬት ፈንድ ለጋሽ ሀገራት ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።




ኮሚሽኑ በአዲሱ የ5 ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ የታያዙ ዋና ዋና ተግባራትን አከናውኖ ውጤት ለማምጣት የድጋፉ መቀጠል አስፈላጊነትም አያጠያይቅም ብለዋል።


ኮሚሽኑ ተቋማዊ አደረጃጀትና የመፈፀም አቅሙን እያጠናከረ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣትም ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ኮሚቴው ውይይቱን ለ2027 በጀት ዓመት የተያዙ ዕቅዶች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል።