ሽግግር ፍትሕ
እውነትን መፈለግ
ያለፉ ወንጀሎችን እና መንስዔዎቻቸውን ለማጣራት የሚያስችሉ አሠራሮችን በመዘርጋት የተጎጂዎችን እውነትን የማወቅ መብት ማረጋገጥ
ፍትሕ
የመብት ጥሰቶችን በሕግ ሂደት እንዲታዩ በማድረግ፣ የሕግ ማነቆዎችን በማስወገድ እና ለዘላቂ እርቅ ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ፍትሕን ማስከበር
ካሳ እና መልሶ ማቋቋም
ካሳ እና መልሶ ማቋቋም ለተጎጂዎች የገንዘብ እና ገንዘብ ነክ ያልሆኑ ክሳዎችን፣ ማቋቋምን፣ ወደነበሩበት መመለስን እና መታሰቢያዎችን ማቆምን ጨምሮ ተገቢውን የመብት ጥሰት ማካካሻ ማረጋገጥ ነው
መታሰቢያ ማቆም
ለተጎጂዎች እውቅና ለመስጠት፣ ሕብረተሰቡን ለማስተማር፣ ቁስልን ለማዳን እና የወደፊት የመብት ጸቶችን ለመከላከል ያለፉ ጥሰቶችን ትክክለኛ መረጃዎች ተብቆ ማቆየት
ዳግም እንዳይከሰቱ የሚሰጡ ዋስትናዎች
የግጭት እና የመብት ጥሰቶች ስረ-መንስዔዎችን ማስወገድ እንዲሁም ለዘላቂ ለውጥ አሳታፊ የሆነ ተወካይነትን ማረጋገጥ

በሽግግር ፍትሕ ሂደት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሚና ምንድን ነው?
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ለማስፋፋት እና ለመጠበቅ በሕግ ሥልጣን የተሰጠው ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋም እንደመሆኑ መጠን፤ አግባብነት ያላቸውን የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች እና መስፈርቶች መሠረት በማድረግ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ አቀራረብን በመከተል በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና በሰብአዊነት ላይ ለተፈጸሙ ከባድ ጥሰቶች የተጠያቂነት እርምጃዎች እንዲወሰዱ በመሞገት ረገድ በግንባር ቀደምትነት ሲሠራ ቆይቷል።
Latest News & Updates
No posts
-
በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ትግበራ የማኅበረሰብ መሪዎችን የነቃ ተሳትፎ ለማረጋገጥ ያለሙ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን ቀጥለዋል
ስልጠናዎቹ የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ በሰብአዊ መብቶች መርሆች ላይ ተመስርቶ ፍትሐዊና ዘላቂ ውጤት እንዲያመጣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው
-
ኢሰመኮ በሽግግር ፍትሕ ላይ የአካባቢ ማህበረሰቦችን ግንዛቤ ለማጎልበት ከኢትዮጵያ እድሮች ኅብረት ማህበራዊ ተቋም ጋር በጋራ ይሠራል
ከማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች ጋር መተባበር በሽግግር ፍትሕ ሂደት የህዝብ ተሳትፎን ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና ይጫወታል
-
አድሎአዊ የዘር ልዩነቶችን ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት (ICERD) አፈጻጸምን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ረቂቅ የተጠቃለሉ ሪፖርቶች ላይ የተካሄደ ምክክር
ሪፖርት የማቅረብ ግዴታዎችን በወቅቱ መወጣት፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች አፈጻጸምን ለመገምገም ወሳኝ ነው
-
በኢትዮጵያ አካታች የሽግግር ፍትህ ሂደትን ለመደገፍ በሚደረጉ የጋራ ተግባራት ዙሪያ የተፈረመ መግባቢያ ሰነድ
ተጎጂዎችን ያማከለ እና ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲኖር ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ያለውን አጋርነት ማጠናከር ያስፈልጋል
No posts
No posts
No posts

Sign up for our bimonthly newsletter to receive updates on Transitional Justice (TJ)-related events organized by various stakeholders across Ethiopia
