ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ለአደጋ የተጋለጡ እና ብዙውን ጊዜ ለመብቶቻቸው መከበር የተለየ ድጋፍ እና ጥበቃ ካልተደረገ ለተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የመዳረጋቸው ዕድል የሰፋ ነው
በየዓመቱ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ በኢሰመኮ አዘጋጅነት የተጀመረው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል፤ በቀጣይ ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ለሦስተኛ ዙር የሚመለስ ይሆናል
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የክልል ሰንደቅ ዓላማን የመስቀል እና ክልላዊ መዝሙርን የማስዘመር እርምጃ የሕግ መሠረት የሌለው ነው ሲል ኢሰመኮ ገለጸ
የየትምህርት ቤቶቹና አጠቃላይ ማኅበረሰቡ በሰላም፣ በመቻቻል እና የሃሳብ ልዩነትን በመቀበልና በሰላማዊ መንገድ ብቻ በመፍታት ላይ ተመሥርቶ የመፍትሔ አካል እንዲሆን አበክሮ ያሳስባል
እነዚሀ ህጻናት ለተለያየ ጊዜ በእስር መቆየታቸው “ተገቢ ያልሆነ እና ለተፈጠረው ውዝግብ እና ግጭት ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ” መሆኑን ኢሰመኮ ረቡዕ ታኅሣሥ 19/2015 ዓ.ም. ባወጣው የምርመራ ሪፖርት አስታውቋል
በእውነተኛ የሕይወት ገጠመኞች ላይ የተሰሩ ፊልሞች አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ለእይታ ቀርበው በችግሮች መነሻ እና በመፍትሔውም ላይ ውይይት ተደርጎባቸዋል
ዘንድሮ ከመጀመሪያው ዙር በተለየ መልኩ በተለያዩ አምስት ከተሞች በተለያዩ ቋንቋዎች የተሰሩ ፊልሞችን በመተርጓም፣ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የተሟላ መረጃ የያዘ እና በየጊዜው ወቅታዊ የሚደረግ የአመዘጋገብ ሂደት ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል
የሠራተኞች መብቶችን አፈጻጸም በበላይነት የማረጋገጥ ኃላፊነት የመንግሥት ቢሆንም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም ኢሰመኮ በክትትል ሪፖርቱ ያቀረባቸውን ምክረ-ሃሳቦች ለመተግበር በጋራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል
ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተመሳሳይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ወደፊትም እንዳያጋጥሙ ለችግሩ መንስኤ ለሆነው የሰንደቅ ዓላማ እና መዝሙር ውዝግብ ሕፃናትን ጨምሮ ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ ግልጽ የሆነ የሕግ እና ፖሊሲ መፍትሔ በማበጀት ዘላቂ እልባት መስጠት ይኖርባቸዋል