የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘር ማጥፋትን መከላከል ልዩ አማካሪ ቢሮ፤ በቀጣናው የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል
በዚህ ሳምንት የአንድ ለአንድ ዝግጅት በአሳሳቢው የሴቶች ጥቃት ላይ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ እንግዳ አድርጓል
ለተፈናቃዮች የሚቀርበው ሰብአዊ ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን እና የጾታዊ ጥቃት ሥጋቶች መበራከታቸውን ኢሰመኮ ገለጸ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ የሪጅን ዳሬክተር የሆኑት ሰላማዊት ግርማይ ኢሰመኮ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ስለሚያከናውናቸው ተግባራት፤ እንዲሁም በዋነኝነት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ ክትትልና ምርመራ በማድረግ ለጥሰቶቹ መፍትሔ ለማፈላለግ የሚያከናውናቸውን ተግባራትና ስለሚሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች አስረድተዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ያሉበት ሁኔታ ሳይገለጽ በተራዘመ እስር ውስጥ የሚገኙ በአስገድዶ መሰወር ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ከ52 በላይ ሰዎች አቤቱታ መመርመሩን፤ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተራዘመ እስርና አስገድዶ በመሰወር ከ1 እስከ 9 ወራት አስረው ያቆዩዋቸው ሰዎች መለቀቃቸውን በመግለጫው አትቷል
ከነበሩበት ቀዩ ለቀው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከገቡም በኃላ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እንደሚፈጸምባቸው ኢሰመኮ ጠቅሷል
ኢሰመኮ በኢትዮጵያ ካሉት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መካከል 2.2 ሚልዮን ያህሉ በግጭትና ጦርነት የተፈናቀሉ መሆኑን ለአሻም ገለጸ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በቀጠሉ ግጭቶችና የተፈጥሮ አደጋዎች ከ5ሺሕ የሚልቁ ትምሕር ቤቶች ተዘግተው የመማር ማስተማር ሂደቱ መቋረጡን በጥናት ማረጋገጡን አስታወቀ
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚኖሩባቸው ጣቢያዎች “ተገቢ ጥበቃ ስለማይደረግላቸው”፤ የታጠቁ አካላት “ሰርገው በመግባት ጥቃት እንደሚፈጽሙ” የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
በኢትዮጵያ ለተፈናቃዮች የሚደረጉ የሰብአዊ ድጋፍ እና ጥበቃ እንዲሁም የዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ ሥራዎችን የሚያስተባብር እና በበላይነት የሚመራ ተቋም ባለመኖሩ፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ አሳሳቢ ችግር ሆኖ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ