በሴፍቲኔት አገልግሎት ትግበራ ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመፍታት የአረጋውያን የተሟላ ማኅበራዊ ዋስትና የማግኘት መብትን ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሠሩ ይገባል
የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች ውጤታማ አተገባበር የሚወሰነው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ብሔራዊ ተቋማት ባላቸው ጥብቅ ክትትል የማድረግ እና ወቅታዊ ሪፖርት የማቅረብ ዐቅም ላይ ነው
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው፣ የተጎጂዎችን ሰብአዊ መብቶች ያከበረ፣ የተቀናጀ እና አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ አሳስበዋል
ኢሰመኮ የዳኝነት እና የዴሞክራሲ ተቋማት ሰብአዊ መብቶችን ማእከል ያደረጉ አገልግሎቶችን በመስጠት ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን በመፍጠር ሂደት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል
የአካል ጉዳተኞች የሥራ መብት እንዲከበር ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ ያስፈልጋል
ሁለቱ “ደረጃ-ሀ” (A-status) ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ያላቸውን ትብብር በማጠናከር እና እርስ በእርስ በመማማር ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር ያላቸውን የጋር ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በሰዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እና መፈናቀል እልባት ለመስጠት የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል መንግሥታት በዞኑ በቂ የጸጥታ አካላትን ማሰማራትና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ጨምሮ አፋጣኝ፣ ተጨባጭና ዘላቂ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል
ኢሰመኮ እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እና የሰላም ግንባታን በተመለከተ በጋራ ለመሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት (“የጅማ ስምምነት”) ተፈራርመዋል
የተጎጂዎች ማኅበራትን ተሰሚነትና ደህንነት ማጠናከር በሽግግር ፍትሕ ሂደት ለሚኖራቸው ትርጉም ያለው ተሳትፎ ጉልህ ሚና ይጫወታል
ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2019 ዓ.ም. የምታዘጋጀው የአፍሪካ ብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት ትስስር (NANHRI) ጠቅላላ ጉባኤ እና በየሁለት ዓመቱ የሚያካሂደውን 16ኛው ኮንፈረንስ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ባለድርሻዎች ቀና ትብብር እና እገዛ እንዲያደርጉ፣ ኢሰመኮ የሚሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበሩ ኢሰመኮ ጥሪ ያቀርባል