የሁኔታ መከታተያው ምርጫው ሰብአዊ መብቶችን ያከበረ መሆኑን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል
ስትራቴጂክ ዕቅዱ ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ ጥበቃ እና መከበር አጋዥ የሆኑ የዲጂታል አሠራርና የፈጣን መረጃ ልውውጥ ሥርዓቶችን አካቶ የተዘጋጀ ነው
የተጠርጣሪዎች አያያዝ ሁኔታ ሰብአዊ መብቶችን ያከበረ መሆኑን በማረጋገጥ ረገድ የፖሊስ ተቋማት ጉልህ ሚና አላቸው
ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት እና ጥበቃ እንዲሁም ውጤታማ የሽግግር ፍትሕ ትግበራ የክልል ሕግ አውጪ፣ አስፈጻሚ እና ተርጓሚ አካላት ሚና የጎላ ነው
የሲቪክ ምህዳርን ለማስፋት እና የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ጥበቃን ለማጠናከር የመንግሥት ቁርጠኝነት፣ የብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት እና የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች የጋራ ሥራ ወሳኝ ነው
በአርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት መብትን ለማረጋገጥ ትምህርትን ከማኅበረሰቡ የኑሮ ዘይቤ ጋር ማጣጣምና ተደራሽነቱን ማረጋገጥ ወሳኝ ነው
ሹመቱ ኢሰመኮ በሰብአዊ መብቶች ዘርፍ ለበርካታ አመራሮችና ባለሙያዎች መፍለቂያ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ ተስፋ ሰጪ እርምጃ ነው
ስልጠናዎቹ ለወጣቶች፣ ለፖሊስ እና ማረሚያ ቤት አባላት፣ ለአረጋውያን፣ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አገልግሎት ሰጪ አካላት፣ ለአካል ጉዳተኞች ማኅበራት እና ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የተሰጡ ናቸው
ወቅታዊ እና ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳዎችን ተገንዝቦ አስተዋጽዖ የማድረግ ዐቅም ያለው ትውልድ በማፍራት ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ይቻላል
የምክትል ዋና ኮሚሽነር እና የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች ኮሚሽነሮች መሾም፣ የአመራር ቀጣይነትን እና የተሳለጠ የሥራ ሽግግርን ከማረጋገጡም በላይ ኮሚሽኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ያለውን ዐቅም ይበልጥ ያጠናክረዋል