



ክትትሉ በዋናነት ያተኮረው በማእከላቱ አደረጃጀት፣ በተጠቃሚዎች ልየታ ሥርዓት፣ በአገልግሎት ዓይነቶች እና በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ ሲሆን፤ አግባብነት ካላቸው ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ሕጎች እና መርሆች አንጻር በመገምገም ምክረ ሐሳቦችን ይሰጣል፡፡ በዚህ ክፍል የክትትሉ አንኳር ጉዳዮች እና ምክረ ሐሳቦች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማድረግ አንዱ በመሆኑ በተለይ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ የክትትል ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ አረጋውያን ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው ለሚመጡ አድሎዎች እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ በመሆናቸው እና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለመስጠት ሲባል አረጋውያንን በአንድ ማእከል ውስጥ አሰባስቦ እንክብካቤ መስጠት...


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) የተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ያለበትን ሁኔታ ለመረዳት፤ የመፈናቀሉ አውድ እና መንስኤዎች፣ በመፈናቀል ወቅት ያጋጠሙ አንኳር የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክፍተቶች እና የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎቶችን ለመለየት ከሐምሌ 24 እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች (ደ/ብ/ብ/ሕ) ክልል በኮንሶ ዞን፣ በአሌ ልዩ ወረዳ፣ በዲራሼ ልዩ ወረዳ እና በአማሮ ልዩ...
ይህ ዓመታዊ የሴቶችና የሕፃናት መብቶች የዘርፍ ሪፖርት ከመስከረም 2014 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 2014 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን ኢሰመኮ ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው አጠቃላይ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በተጨማሪነት በተለይ የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ኮሚሽኑ የለያቸውን አበረታች እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን እና ምክረ-ሃሳቦችን አካቷል፡፡ ኮሚሽኑ...